All Posts


የአማራ ክፍላተሀገር ሕብረት መግለጫ
ከአማራ ክፍላተሀገር ሕብረት የተሰጠ የእንኳን ደስ ያላችሁና የድጋፍ መግለጫ የአማራ ህዝብ ላለፉት ዓመታት ከተጋረጠበት የህልውና አደጋ፣ ከተደገሰለት የዘር ማጥፋት እና ከከፋ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ራሱን ለመከላከል ሲል በመራራና በቁርጠኝነት የጀመረው የአማራ ህልውና ትግል፣ ዛሬ አዲስ ምዕራፍ እና ከፍታ ላይ ደርሷል። ላለፉት ሠላሣ ወራት፣ የፋኖ አደረጃጀቶች በተናጠልና በቡድን በመሆን፣ የአማራን ህዝብ ክብርና ህልውና ለማስጠበቅ እጅግ ውድ የሆነውን ህይወታቸውን ገብረው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው፣ ደማቸውን አፍስሰው ታሪክ የማይረሳው አኩሪ ተጋድሎ ፈጽመዋል። ይሁንና፣ በዚህ መራራ የትግል ጉዞ ውስጥ፣ የዓላማ አንድነት ቢኖርም፣ የአደረጃጀት እና የመዋቅር ልዩነቶች የትግሉን ፍጥነት ሲገቱት፣ የአንድነትን ክንድ ሲያላሉትና ለጠላት ክፍ
4 days ago





